አልሚ ንፁህ ማር፣ ቅቤ እና ባህላው መጠጥ (ጠላ)
1. ማር፡-
ወለላ ማር
የማር እንጀራ አለን
2. ቅቤ፡-
ለጋ ቅቤ
መካከለኛ ቅቤ
3. የጠላ እህል (ጠላ)
አዘገጃጀት ፡-
በመጀመሪያ የጠላውን እቃ በደንብ ማጠብና በወይራ እንጨት ማጠን፣
ለ 1 ኪ.ግ የጠላ ዱቄት በ 1 ሊትር ዉሃ ጨምሮ መደፍደፍ፣
ቢያንስ ድፍድፉ ከተደፈደፈ በኋላ ከ10 ቀን እስከ 12 ቀን ማቆየት፣
ለ1ዱ ኪ.ግ የጠላ ድፍድፍ 3 ሊትር ውሃ ጨምሮ ማሰርና ማሳደር ወይም ማዋል፣
አንዱ ኪሎ ግራም የጠላ ድፍድፍ 3 ሊትር ወፍራም ቆንጆ ጠላ ይወጣዋል፡፡
ሁለተኛ አስሮ ቅራሪ ይወጣዋል፡፡ ውድ ቤተሰቦች ጠላውን ግድ ማሰር አይጠበቅብነም ነገር ግን የጠላው ውጤት ልክ እንደእስሩ ብዙ አይወጣውም ማለትም ሲታሰር ሁሉም ስለሚንጠፈጠፍ አተላው ድርቅ ስለሚል የጠላው ውጤት ይበዛል እና ከለሩም ልክ እንደ ኮካ ከለር ይሆንልናል፡፡ ሲሞላ ግን ጠላው በደንብ ቅርር አይልልንም ስለዚህ ማሰር ይመረጣል ማለት ነው፡፡
ከታሰረ በኋላ ለምሳሌ ጠላው ለከነገወዲያ የሚፈለግ ከሆነ ዛሬ ማታ አስሮ ማሳደር ነገ ሲፈላ ይውልና ለከነገወዲያ በጣም ቆንጆ ጠላ ይሆንላችኋል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ውድ ቤተሰቦች ጠላን በአንድ ጊዜ ደፍድፎ ለረጅም ጊዜ ማቆትና በአስፈለገን ጊዜ በጥብጠን ለመጠጣት ስንፈልግ የምንደፈድፍበትን ውሃ ማሳነስ አለብን
ለምሳሌ 1 ኪ.ግ ጠላ ዱቄት በግማሽ ሌትር ውሃ ጨምረን ልክ እንደበሶ ፍርፍር አድርጎ በወፍራሙ መተውና ንፋስ እንዳይገባው በላስቲክና በልብስ በደንብ ከድነን ማስቀመጥ ከዚያ በኋላ ከሶስት ሳምንት በኋላ ጠላው መድረስ ይችላል ግን የጣላው ጣእም እየቆየ ነው የሚወጣው ቢያንስ አዲድ አበባ ላለ ሰው እስከ 5 ወር ድረስ ማቆየት ይችላል እየቆየ በሔደ ቁጥር የጠላው ጣዕም እየጨመረ ይሔዳል፡፡
4. የኬኔቶ ገብስ
አዘገጃጀት፡- በመጀመሪያ ድስት ውስጥ ጨምረን በደንብ ውሃ ከጨምረን በኋላ እሳት ላይ መጣድ ቆንጆ ሽታ እንዲሰጠን ከተፈለገ ትንሽ የሻይ ቅመም (ቀረፋ) መጨመር ከዚያ በኋላ በደንብ መቀቀል፡፡ ከእሳት ላይ ካወረድነው በኋላ የሚበቃንን ያህል ስኳር መጨመር ከዚያ በማጣሪያ ማጣራትና በአዘጋጀነው እቃ ላይ መጨመር ከዚያ በኋላ አሻሮውን ለሁለተኛ ጊዜ መቀቀልና አጣርተን ትንሽ እርሾ ጨምረን ቢያንስ ለ4 ቀን ያህል ማቆት በጣም ቆንጆ ነው የሚሆንላችሁ ትወዱታላችሁ፡፡
አመሰግናለሁ
5. የሀበሻ አረቄ፡- አረቂው የጎጃም መራዊ ከተማ አረቂ ነው በጣም ትወዱታላችሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ ለበለጠ መረጃ አንዳንድ ቪዲዎችን እለቃለሁ፡፡
6. ቡና
ተቆልቶ የታሸገ
ተፈጭቶ የታሸገ